Ring ring
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

ማሩን ቁረጠው ቀፎውን ግን አትስበረው


እርጋታ በምንም ነገር ላይ ቢፈፀም ያሳምረዋል ፤ ከምንም ነገር ላይ ቢነሳ ደግሞ ያበላሸዋል። በንግግር ላይ ልስላሴ በፊት ላይ ፈገግታ እና ከሰው ጋር ሲገናኙ መልካም ንግግር መናገር ደስተኞች የሚገለፁባቸው መለያዎች ናቸው። የሙእሚንም ባህሪይ ነው። ልክ እንደ ንብ መልካምን በልታ መልካምን ትሰራለች። በአበባ ላይ ስታርፍም አበባውን አትሰብረውም። ምክኒያቱም አሏህ በእርጋታ የሚሰጠውን በጭካኔ አይሰጥም። ገና ሲታዩ አንገቶች ብቅ የሚሉላቸው ፤ ዓይኖቶች የሚርገበገቡላቸው ፤ ልቦች የሚሳሱላቸው እና ነፍሶች የሚሸኟቸው ሰዎች አሉ። ምክኒያቱም በንግግራችው የሚወደዱ ፤ በአሰጣጥ ፣ በአወሳሰዳቸው በአሻሻጥ ፣ በአገዛዛቸውና በአቀባበል በአሸኛኘታቸው እጅጉን የተወደዱ ስለሆኑ።

ጓደኞችን ማፍራት ደጋግና ቅኖች የሚካኑት የተጠና ጥበብ ነው። በመሆኑም ሁሌም ሲመጡ በጫወታና በወግ የሚያንበሸብሿቸው ሲጠፋ ደግሞ የሚናፍቇቸው እና ዱዓእ የሚያደርጉላቸው በርካታ ሰዎች ያካብቧቸዋል። እነዚህ ደስተኞች..........

--<({አል-ቁርአን 41:34})>--

«መልካም በሆነችው ጠባይ(መጥፎይቱን) ገፍትር ፤ ያን ጊዜ ያ ባንተ እና በርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ አዛኝ ዘመድ ይኾናል።»

የሚል ርዕስ ያለውን የባህሪ ፍልስፍና ይከተላሉ። ስለዚህ ጥልቅ በሆነው የእዝነት ስብዕናቸው ምቀኝነትን ያሟሽሻሉ። ሁሌም በትዕግስታቸው እና ይቅርባይነታቸው የሚፈፀሙባቸውን ጥፋቶች ችላ ብለው የተዋሉላቸውን መልካም ነገሮች ብቻ ያስታውሳሉ። መጥፎ ቃላት ሲወረወሩባቸው ጆሯቸውን ሳይጠጉ ራቅ ብለው ይወድቃሉ። መመለሻም አይኖራቸውም። እነሱ ሁሉም እረፍት ውስጥ ናቸው ፤ ሰዎችም ከነሱ ተጠብቀዋል ሙስሊሞችም ሰላም አግኝተዋል።

--<({አል-ቁርአን 3:134})>--

«ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች»

እነዚህን ሰዎች የልብ እርጋታንና የህሊና እረፍትን ፣ መረጋጋትን የመሳሰሉ ፈጣን ምንዳ እንደሚያገኙ አብስራቸው። በመጨረሻውም ዓለም መሃሪ በሆነው ጌታ ዘንድ ታላቅ ምንዳ እንደሚጠብቃቸውም አብስራቸው።
ቻይ የሆነው ንጉስ ዘንድ በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈልቁባቸው ጀነቶች እንደሚጠብቇቸውም ንገራቸው።


268

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ